ከሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

ከሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን እየተባባሰ የመጣው የኢትዮጵያ ሁኔታ በጣም እንዳሳሰበው ይገልጻል፡፡ እየተፋፋመ  የሚሄድ  ዉጊያ እና የሠዎች መሰደድ ለተረጋጋ አኗኗር  አስተዋፅኦ አርጎ አያዉቅም::

ይህ ክስተት ኮቪድ-19 ካስከተለው የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ተጽእኖ ጋር ተደምሮ፣ ኢትዮጵያ እስካሁን ያሳካችውና በ2020 (እ.አ.አ) በተደረገው የኢብራሂም የአፍሪካ መልካም  አስተዳደር ደረጃ ያስመሰከረችው  መሻሻል፣ እንደገና የመቀነስ አዝማሚያ እንዲጋረጥበት አድርጎታል፡፡ 

የሞ ኢብራሒም ፋውንዴሽን ሁሉም አካላት  ወደሰላማዊና የኃላፊነት ስሜት ወደሚንፀባረቅበት  መንገድ እንዲመለሱ ጥሪውን ያቀርባል፡፡ 

ይህ  ችግር የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ዜጎች የተሻለና የጋራ ፍላጎት አሟልቶ፣ እንዲሁም በብዙ ጥረት የተገኘውን ግን ደግሞ በቋፍ ያለውን የቀጠናውን መረጋጋት ጠብቆ፣  መፍትሔ ሊያገኝ የሚችለው  በውይይትና ንግግር ብቻ ነው፡፡